በማገገም ላይ የሚገኙ ቁስለኞችን ጎብኝት

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ ሆስፒታል በማገገም ላይ የሚገኙ ቁስለኛ የሰራዊት አባላትን ጎበኙ።
ቁስለኞችንም “የሀገራችሁን ክብር በማስቀደም የከፈላችሁት የአካል መስእዋትነት በታሪክ መዝገብ ውስጥ ተቀምጦ ለዘላለም ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል” ሲሉ አበረታተዋል።
በህክምና ላይ የሚገኙ ቁስለኛ የሰራዊት አባላትም ለሀገራቸው ክብር የከፈሉትን ዋጋ ትልቅ ቦታ በመስጠት ሚኒስትሩ ስለጎበኟቸው ደስተኛች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ተገኝ ለታ ከጦር ኃይሎች ኮንፕሪሄንሲቭ ሆስፒታል፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከአለርት ሆስፒታል እና ከሌሎችም አጋር አካላት ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ በማግኘት ለታካሚዎቹ ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ላይ መሆኑን አሳውቀዋል።