በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ እየሰሩ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ያሰባሰበ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ እየሰሩ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ያሰባሰበ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው፡፡
በአፍሪካ ለ17ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ጉባኤው በአኅጉሪቱ በሚገኙ 5 ታላላቅ ከተሞች ማለትም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ፣ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ፣ በሴኔጋል ዳካር፣ በናይጄሪያ አቡጃ እና በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው ከአፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች በየቀጣናው እየተሳተፉ ነው።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን ጉባኤ አይ ኤም ኤስ ፎጆ (IMS –FOJO) ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዊውተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
የአይ ኤም ኤስ ፎጆ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ሶፊ ጉልልበርግ ጉባኤው በአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኞችን አቅም በሥልጠና ለማዳበር የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የምርመራ ዘገባዎችን የሰሩ ጋዜጠኞች ልምዳቸውን እያጋሩ ይገኛሉ፡፡
በሳልሳዊት ባይነሳኝ