በርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ጥር 9/2014 (ዋልታ) በሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የተመራ የልዑካን ቡድን ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገባ።

በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች የሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ልዑኩ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉንም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ የተረከቡ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ ከሶማሌ ክልል መንግስት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።