በሰሜን ሸዋ ዞን በሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት

መስከረም 9/2014 (ዋልታ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሁለተኛ ዙር የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች በደብረ ብርሃን ከተማ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረጻዲቅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገር መሪዎች የሚፈሩበት ተቋም በመሆኑ ወጣቶቹ ይህንን ተቋም ለመቀላቀል በመወሰናቸው ሁሌም የሚኮሩበት ነው ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ “እናንተን የመሰሉ ደፋርና ጀግና ወጣቶች ስላሏት ከጉዞዋ ሊያስቀራት የሚችል አንዳች ኀይል አይኖርም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሌሎች ወጣቶችም የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ሸት ከተደረገላቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ተስፋሁን አየልኝ “እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሚንቀሳቀስ ሁሉ ከሀገራችን በፊት መስዋእት ለመሆን ዝግጁ ነን” ብሏል፡፡

ወጣት ሸዋንግዛው ይልማ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዘብ እንድንቆም ይህንን እድል በማግኘታችን ደስተኞች ነን ብሏል፡፡