በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች እፎይታ ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ

የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል

ግንቦት 21/2014 (ዋልታ) በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና ለዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው።

በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።

ማዕከሉ በነገው ዕለት እንደሚመረቅም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦ ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW