በሳይንስና ፈጠራ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – በሳይንስ፣ ፈጠራ እና ሀገር በቀል እውቀት ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

አውደ ጥናቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ ከ23 የሚደርሱ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

በሳይንስና ፈጠራ እንዲሁም ሀገር በቀል እውቀት ላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከምርምር ተቋማትና ማዕከላት እንዲሁም ከዞንና ወረዳ የተውጣጡ ከ400 በላይ ባለድርሻ አካላት በአውደ ጥናቱ ተሳታፊ ይሆናሉ።

(በሳራ ስዩም)