በስዊዘርላንድ ለተጎዱ ወገኖች ከቶምቦላ ሎተሪ 35 ሺሕ የስዊዝ ፍራንክ ተሰበሰበ

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ኅብረት በሰዊዘርላንድ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመርዳት “የገና ስጦታ ለእናት አገሬ” በሚል ያዘጋጀው የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ የማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ።
በዚህም በሽብር ቡድኑ ትሕነግ ጥቃት ለተጎዱ ወገኞች የሚውል 35 ሺሕ የስዊዝ ፍራንክ ተሰብስቧል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በስዊዘርላንድና ጄኔቫ በሚገኙ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር በአገር ሉኣላዊነትና በሕዝብ ደኅንነት ላይ ጥቃት ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በአገር ፍቅርና በፍጹም ኢትዮጵያዊ አንድነት ስሜት የታየው ቁጭት፣ መነሳሳትና ተሳትፎ እጅግ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡