በሶማሌ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) ከሶማሌ ክልል የተወከሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሶማሌ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳሰቡ፡፡

የምክር ቤት አባላት ሰሞኑን በከልሉ በፋፈን ዞን አውበሬ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ የጎብየሬይ፣ የአባይፉላን እና አንፋርታ ቀበሌዎች ማኅበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው ማሳሰቢያ የሰጡት።

በውይይቱ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ የተገመገመ ሲሆን ማኅበረሰቡ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር፣ የመብራት አገልግሎት አለመኖር፣ በጎብየሬይ ትምህርት ቤት በቂ አስተማሪ እና ግብዓት አለመኖር፣ ኑሮ ውድነት እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦት እጥረትና ጤና ጣቢያ አለመኖር በስፋት ያነሷቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቁሟል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በየቀበሌዎቹ የሚታዩትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከተው አስፈፃሚ አካል ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW