በሶማሌ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቋቋመ

ጥቅምት 25/2014 (ዋልታ) በሀገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ከትናንት በስቲያ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማስፈጸም በክልሉ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራ ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡