በቦስተን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ከ117 ሺሕ ዶላር በላይ ለገሱ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ ቦስተን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው ሕወሓት ወረራና ጥቃት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ከ117 ሺሕ ዶላር በላይ ለገሱ፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በድጋፍ ማሰባሰብ ሂደቱ የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ ለጋስ ኢትዮጵያዊያን መሳተፋቸውን ጠቅሰው አመስግነዋል፡፡
‹‹ለወገን ደራሽ ወገን ነው›› በሚል እሳቤ የሚካሄደው የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብርም በሌሎች ግዛቶች በተመሳሳይ ዝግጅቶች መቀጠሉን ጠቁመዋል፡፡