በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችና 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በጥናት ላይ ተመስርቶ ባደረገው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን እና 33 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ፡፡

ተሽከርካሪዎቹ እየተሰረቁ አብዛኞቹ ወደ ሀዋሳ ከተማ እንደሚወሰዱ በምርመራ ማረጋገጥ እንደተቻለ ተነግሯል፡፡

ከተሰረቁት ተሽከርካሪዎች መካከል ሰባቱ በአዲስ አበባ የተገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ 15  ተሽከርካሪዎች ደግሞ በሀዋሳ ከተማ እና ከሀዋሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ተይዘው እንዲመለሱ መደረጉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ተሽከርካሪ በመስረቅ፣ የተሰረቀውን ተሽከርካሪ በመግዛት እና በመደለል ተሳትፎ ያደረጉ ከአዲስ አበባ 19፣ ከሀዋሳ ደግሞ 14 በአጠቃላይ 33 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል፡፡