በአለም ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ያለምዘርፍ ሪከርድ በመስበር አሸነፈች

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – በሰሜን አየርላንድ በተካሄደ የአለም ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ሪከርድ በመስበር አሸነፈች፡፡

ዘንድሮ ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደው ውድድር በሴቶች ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት ተሳታፊ የነበረችው አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸንፋለች፡፡

ያለምዘርፍ ርቀቱን በበላይነት ስታጠናቅቅ አንድ ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባታል፡፡

የገባችበት ሰዓትም የአለማችን የርቀቱ ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ከዚህ ቀደም ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንጌትች የዚህ ርቀት ክብረወሰን ባለቤት የነበረች ሲሆን ያለምዘርፍ በአስራ ዘጠኝ ሴኮንድ በማሻሻል ነው ሪከርድ ልትሰብረው የቻለችው፡፡

በወንዶች ምድብ በተካሄደ ውድድር ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል፡፡

ግማሽ ማራቶኑን ጀማል ይመር በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ አካልነው ተስፋሁን ሁለተኛ ሆኗል፡፡

ኬንያዊው ኪሚንግ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ርቀቱን ፈፅሟል፡፡