የካቲት 10/2013 (ዋልታ) – የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት በነጻ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ የሚሰጠው ከየካቲት12 ቀን እስከ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ተብሏል፡፡
ቢሮው ከጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከፕሮጀክት ሃረር ኢትዮጵያና ከስማይል ትሬን ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር አገልግሎቱን እንደሚሰጥ ገልጿል።
ለከንፈር መሰንጠቅ እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለላንቃ መሰንጠቅ ከ2 ዓመት እድሜ ጀምሮ ችግር ያለባቸውን ህጻናትና አዋቂዎች የነጻ ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል ፡፡