በአሜሪካ የመሪላንድ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ኢትዮጵያ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ 2 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ

በአሜሪካ የመሪላንድ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ኢትዮጵያ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – በአሜሪካ የመሪላንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወይዘሮ ኢትዮጵያ አልፍሬድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ኩራት እንደሚሠማቸው በተደጋጋሚ የሚገልጹት ወይዘሮ ኢትዮጵያ ለህዳሴ ግድቡ ድጋፍ ያደረጉበትን የ2 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ቼክ በስጦታ መልክ አስረክበዋል፡፡ ይህም አሁን ባለው የዶላር መሸጫ ዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ወደ 89 ሺህ ብር ገደማ ይሆናል ተብሏል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት፣ ወይዘሮ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን በጨዋ ደንብ ምርጫ በማከናወናቸው የተሰማቸውን ኩራትና ደስታም ገልጸዋል፡፡