በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች #NoMore ንቅናቄ ሰልፍ ተካሄደ

ታኅሣሥ 11/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ግዛቶች የበቃ #NoMore ንቅናቄ አካል የሆነ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
በግዛቶቹ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት እና የሀሰት የሚዲያ ክስ በመቃወም ነው ዘመቻውን ያደረጉት፡፡
በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አንዳንድ ምእራባውያን አገራት በቀጥታና በሌሎች ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እንዲሁም በመገናኛ ብዙኃኖቻቸው በኩል በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱት ያለውን ተፅእኖ እንዲያቆሙ የሚጠይቁ ሰልፎች በመላው ዓለም መካሄዳቸው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡