በአምቦ ከተማ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን የአምቦ ከተማ የአስተዳደርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የዘንድሮ ምርጫ የሕዝብ ሠላምና ፀጥታ የተረጋገጠበት እንዲሆን፣ ምርጫውም በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካድ የሚያስችል አስተማማኝ ሰላም በከተማዋ መረጋገጡን የአምቦ ከተማ የአስተዳደርና ፀጥታ ጽህፈት ኃላፊ ባይሳ ሁሴን ገልፀዋል።

ኃላፊው ከተማዋ በአስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው፤ ከፌደራል፣ ክልልና ከተማ አስተዳደር ፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን  የገለፁት የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ፣ የከተማዋ ህዝብም ያለምንም ስጋት በሀገራዊ ምርጫው ድምፁን መስጠት የሚያስችለው አስተማማኝ ሰላም ተረጋግጧል ብለዋል።

6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከማህበረሰቡ ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

(በደረሰ አማረ)