በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምጽ እየሰጡ ነው

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምጽ ለመስጠት ቢሰለፉም ወረፋ ስላልደረሳቸው ድምጽ ለመስጠት መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

የጣቢያው ምርጫ አስፈጻሚ በበኩሉ መራጮች በድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰአት በመጠቀመቸውና በተፈጠረው የምርጫ አስፈጻሚ እጥረት ምክንያት ሂደቱ የተጨናነቀ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

በምርጫ ጣቢያው 1ሺህ 500 መራጮች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸው ታውቋል፡፡

(በብርሃኑ አበራ)