በአርሲ ነጌሌ ከተማ 52 የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኅዳር 7/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አርሲ ነጌሌ ከተማ 52 የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአርሲ ነጌሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጣቢያ ምክትል ኃላፊ ሳጂን ኦላና ገመቹ እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በጸጥታ ኃይሎች በተደረገ ፍተሻ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አልባሳት፣ ኤስ ኬ ኤስ የጦር መሳሪያ፣ የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ የባንክ ደብተሮች፣ የባንክ ቼክ፣ የተለያዩ ሞባይሎችና ላፕቶፖች፣ የተለያዩ መታወቂያ ወረቀቶች፣ መንጃ ፍቃዶችና ከተለያዩ የጽሑፍ መረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  ከአርሲ ነጌሌ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡