በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች በዛሬው እለት ትምህርት መጀመሩ ተገለጸ

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች በዛሬው እለት ትምህርት መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በደማቅ ሁኔታ መጀመሩን የገለጸው ሚኒስቴሩ የትምህርት ዘመኑ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የ2015 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና መመሪያ አስተላልፈዋልም ነው የተባለው፡፡

የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ የሚከናወነውም በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW