በአወስትራሊያ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) በአወስትራሊያ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያንና ሌሎች የወዳጅ አገራት ዜጎች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።
የ#Nomore (በቃ) ንቅናቄ አካል የሆነው ሰልፉ በፐርዝ ምዕራብ አወስትራሊያ ነው የተካሄደው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚጠቁመው ሰልፈኞቹ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እና በተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በፅኑ ተቃውመዋል።