በአዋሽአርባ የወታደሮች ምርቃት

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) በአዋሽአርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮችን አስመረቀ።

ተመራቂ ወታደሮች በቆይታቸው አስተማማኝ ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ የውጭ ሃይሎችንና የውስጥ ከሃዲዎችን ለመመከት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን አሸባሪ የህውሃት ቡድን እስከ ወዲያኛው እንደመስሰዋለን ብለዋል።

በምርቃት ስነ ሥርአቱ ላይ የምድር ኃይል ምክትል አዛዥ የሰው ሃብት ልማት ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።