በአዲስ አበባ በአንድ ጀምበር 4 ሚሊየን ችግኝ ነገ ይተከላል

ችግኝ የመትከል መርኃ ግብር

ነሐሴ 11/2014 (ዋልታ) በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር አራት ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርኃ ግብር እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ መርኃ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በዕለቱም ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በየክፍለ ከተማው ለችግኝ መትከያ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ደማቅ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW