በአዲስ አበባ የቅድመ መጀመሪያና ከ1ኛ- 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት ይጀምራሉ

አቶ ዘላለም ሙላቱ

በ4ኛ ዙር የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም ከሰኞ ጀምሮ በ4ኛ ዙር በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት እንደሚጀምሩ የቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አስታውቀዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማሩ ሂደት እየመጡ በመሆኑ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በአግባቡ መተግበር እንዲቻል ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውንም ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡