በአዲስ አበባ የተለያዩ መሳሪያዎች ትቦ ውስጥ ተጥለው ተገኙ

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ጠመንጃ ያዥ አካባቢ የተለያዩ መሳሪያዎች ትቦ ውስጥ ተጥለው ተገኙ።
ከተገኙት ውስጥ 1 ታጣፊ ከላሽ ብዛት 1 የውግ ቁጥር 24096 የጥይት ብዛት 114 እና 4 ካዝና ይገኝበታል፡፡
1 ማካሮፍ ሽጉጥ ብዛት የውግ ቁጥሩ የማይታይ የጥይት ብዛት 7 ፍሬ እንዲሁም አንድ ጊሌ የሚመስል ሳንጃ ሲሆን ትናንት ኅዳር 17 ተገኝቶ ላንቻ ለፖሊስ ጣቢያ ገቢ ሆኗል።
ፖሊስ ሕብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲቃኝና የተለየ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ እንዲያመለክት ጥሪ አቅርቧል።