በአፋር ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ ነው

ጥር 24/2014 (ዋልታ) በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪው ሕወሓት በፈፀመው ወረራ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ፈተና መውሰድ ጀምረዋል፡፡
ለ3 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ፈተና በሰመራ ከተማ በሚገኘው የሰመራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በአፋር ክልል አሁንም አሸባሪው ወረራ እየፈፀመ እና በንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን በዚህም በሁለተኛው ዙር ፈተና ላልተገኙ በቀጣይ እንዲወስዱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማር ዳይሬክተር ወልዶ ሀይሰማ ገልፀዋል።
በቀጣይ በክልሉ አሸባሪው በከፈተው ጦርነት ምክንያት ተማሪዎቹ የሥነ-ልቦና ችግር እንዳይገጥማቸው ሁለት መቶ ለሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የሥነ-ልቦና ትምህርት እንደሚሰጥ መገለጹን የአፋር ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መረጃ ያመለክታል።