በአፋር ክልል የሰለጠኑ የሚሊሻ አባላት መመረቅ

ጳጉሜ 3/2013 (ዋልታ) በአፋር ክልል የሰመራ ከተማ አስተዳደር ያሰለጠናቸውን የሚሊሻ አባላት እያስመረቀ ነው፡፡

ከ550 በላይ ተመራቂዎች በሰመራ ከተማ አስተዳደር ብቻ የሚገኙ ሲሆኑ በሌሎች የአፋር አከባቢዎች በቅርብ ጊዜያት ከ10 ሺሕ በላይ ሚሊሻዎች ተገቢውን ሥልጠና ወስደው መመረቃቸውን የክልሉ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አይዳሂስ አፍክኤ ገልጸዋል፡፡

ሚሊሸና ልዩ ኃይሉን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ሥልጠናው ቀጣይነት እንዳለውም ተገልጿል።

በተስፋዬ አባተ