በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ማምሻውን በካናዳ ቶሮንቶ ይካሄዳል

ኅዳር 3/2014 (ዋልታ) ምዕራባዊያን አገራትና መገናኛ ብዙኃናቸው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሀሰት መረጃ ዘመቻ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ማምሻውን በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ይካሄዳል።
“የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቶሮንቶና በአካባቢው” አባል ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለሚካኤል ሰልፉ ዛሬ በኢትዮጵያዊያን ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በካናዳ ቶሮንቶ በሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ አጠገብ እንደሚካሄድ ለኢዜአ ገልጿል።
በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ቶሮንቶ መግባታቸውን ተናግሯል።
ሰልፈኞቹ አሜሪካ፣ካናዳ እና ሌሎች ፅኝፈኛ ምዕራባዊያን አገራት መገናኛ ብዙኃናቸውን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን የሐሰት መረጃ ዘመቻ እንዲያቆሙ ጥሪ ያቀርባሉ ብሏል።