በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሴቶችን የሚዘክር መርሃግብር እየተካሄደ ነው

የካቲት 30/2013 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሴቶችን የሚዘክር መርሃግብር እየተካሄደ ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር 125ኛውን የአድዋ ድል ማጠቃለያና የሴቶች ቀንን በማስመልከት ባዘጋጀው መድረክ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ሚና የነበራቸው ሴቶች ተዘክረዋል።

መድረኩ ከዚህ ቀደም ታሪክ ሰርተው ያለፉ ሴቶችን መዘከርና የዚህ ዘመን ሴቶችም የራሳቸውን ታሪክ በመስራት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ማነቃቃትን ዓላማው ማድረጉ ተነግሯል።

በመድረኩ የከዚህ ቀደሙንና የአሁኑን የሴቶች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ የሚያሳይ ሰነድ የቀረበ ሲሆን፣ በሴቶች ለተሰሩ ትላልቅ ስራዎች እውቅና መስጠት ላይ ዳተኝነት መኖሩ ተጠቅሷል።

“የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ዓድዋ እንደ ማሳያ” በሚል መሪ በሚካሄደው በዚህ መድረክ የባህልና ቱሩዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እፀገነት መንግስቱ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ እና ሌሎችም የመንግስት ሴት ከፍተኛ አመራሮችና እንግዶች ተገኝተዋል።

(በትዕግስት ዘላለም)