በኤምባሲው አስተባባሪነት ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ከአቡዳቢ የኢትዮጵያዊያን ኮሙዩኒቲ ማሕበር፣ ከኩፖን ሽያጭ፣ ከሚስዮኑ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

ለድጋፉ ከአቡዳቢ የኢትዮጵያዊያን ኮሙዩኒቲ ማሕበር 274 ሺሕ ዶላር፣ ከኩፖን ሽያጭ 274 ሺሕ ዶላር፣ የሚስዮኑ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች ከመስከረም ወር ደመወዛቸው ለማዋጣት ቃል የገቡትን 20 ሺሕ 567 ዶላር ጨምሮ በድምሩ 568 ሺሕ 512 ዶላር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል።

በዱባይ የኢትዮጵያዊያን ኮሙዩኒቲ ማሕበርም የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የኢፌዴሪ ሚሲዮኖችም በተመሳሳይ ሁኔታ ሀብት በማሰባሰብ ላይ እንዳሉ ይታወቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW