በእውቀት የታነጹ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ተናገሩ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በእውቀት፣ በክህሎትና በራስ መተማመን የታነጹ፣ ለሚቀጥለው የመሪነት እርከን ዝግጁ የሆኑ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ፡፡

5ኛ ዙር ፕሬዚዳንታዊ የሴቶች የመሪነት ሥልጠና መርኃ ግብር 35 ሠልጣኞችን በማስመረቅ ተጠናቋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ “በእውቀት፣ በክህሎትና በራስ መተማመን የታነጹ ለሚቀጥለው የመሪነት እርከን ዝግጁ የሆኑ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ ነው” ብለዋል።

ከጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን 143 በመካከለኛ የመሪነት እርከን ላይ ያሉ ከመንግሥት፣ ከሲቪል ማህበረሰብና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ ሴቶች መሳተፋቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡