በኦሮሚያ ክልል የኮቪድ 19 ክትባት በዘመቻ መልክ ከኅዳር 13 ጀምሮ ይሰጣል

ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ ከኅዳር 13 እስከ 22 እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ኮቪድ 19 እያደረሰ ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና ለመቋቋም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኅብረተሰቡ የተሳሳተ ግንዛቤ በማረም ክትባቱን እንዲወሰድ ታሳቢ ያደረገ ውይይት በቢሾፍቱ ከተማ አድርጓል።

በክልሉ 2.6 ሚሊየን የክትባት መጠን ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ክትባቱ በ19 ከተሞች እና በ12 ዞኖች ዕድሜያቸው 12 ዓመት ጀምሮ ላሉ ታዳጊዎች ይሰጣል ተብሏል ።

የጤና ሚኒስቴር በ65 ከተሞች የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል።

 

በሚኪያስ ምትኩ