በካሊፎርኒያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን 4 ጤና ጣቢያዎች ሊገነቡ ነው

ጥር 24/2014 (ዋልታ) በካሊፎርኒያ ቤይ ኤርያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ክልል ያወደማቸውንና ጉዳት ያደረሰባቸውን አራት ጤና ጣቢያዎች ለመገንባት ወይም ለማደስ መስማማታቸው ተገለጸ።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ “በካሊፎርኒያ ቤይ ኤርያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እስካሁን ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኤምባሲያችን ጋር በመነጋገር 4 ጤና ጣቢያዎችን ለመገንባት/ለማደስና ቁሳቁስ ለማሟላት ተስማምተዋል” ብለዋል።
አምባሳደር ፍጹም ሌሎችም የእነሱን ፈለግ እንደሚከተሉ እምነታችን ነው ሲሉም በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
እድሳትና ግንባታ የሚካሄድላቸው ጤና ጣቢያዎቹ በዋግህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማና ዙሪያ ወረዳ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ሀርቡ ወረዳ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል።