በካርዳችን ዴሞክራሲን፣ በእጃችን ችግኞችን እንትከል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጪው ሰኔ 14/2013 በካርዳችን ዴሞክራሲን፣ በእጃችን ችግኞችን እንትከል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረንጓዴ ዐሻራችንን በማሳረፍ ኢትዮጵያን ለማልበስ የሚደረገውን ጥረት መቀላቀል እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዕለቱ ዝግ እንደሚሆኑ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እሱንም ለማካካስ ቀጥሎ በሚመጣው ቅዳሜ ወደሥራ የምንገባ ይሆናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡