በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት 4.7 ሚለየን ብር ድጋፍ አደረገ


ጥር 27/2014 (ዋልታ) በካናዳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት በካናዳ ከሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች ያሰባሰበውን 4 ሚለየን 750 ሺሕ ብር ለቪዥን ፎር ኢትዮጵያ አስረክቧል።
ቪዥን ፎር ኢትዮጵያ ከኅብረቱ የተረከበውን 4 ሚለየን 750 ሺሕ ብር በጦርነቱ ለተጎዱ ለአማራና አፋር ክልል ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ለመጠገን እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡
ቪዥን ፎር ኢትዮጵያ አሶሴሽን በጦርነቱ ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ህፃናት ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ተነግሯል።
በዙፋን አምባቸው