በክልሉ ለአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ቅድመ ዝግጅት ተደረገ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄቶሳ ወረዳ ዳያ ዳበሶ እና ጉሪ ቀበሌ በሚቀጥለው ወር ለሚካሄደው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ቅድመ ዝግጅት ተደረገ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኤልያስ ከድር በክልሉ በድርቅ እየተጎዱ ለሚገኙት አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የተፈጥሮ ደን ጥበቃ እና ችግኝ ተከላ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው በአየር ለውጥ ምክንያት ድርቅ እንዳይፈጠር ችግኝ መትከል እና የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አስቴር ጌታሁን (ከአርሲ ዞን)