በክልሉ እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጠላትን ቅስም የሰበረ ነው ተባለ

ግንቦት 24/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጠላትን ቅስም የሰበረ መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫቸው የአማራ ክልል ሕግ የማስከበር ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

የውስጥ ስርዓት አልበኝነትን የማስቆም ሥራ የወገንን ኃይል ያጠናከረ የጠላትን ኃይል ቅስም የሰበረ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የሕግ ማስከበሩ ተግባር ሕገ-ወጥነትንና ስርዓት አልበኝነትን መልክ የማስያዝ ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል።

የሕግ ማስከበር ሥራው ለውጭ ጠላት ከሚደረገው ዝግጅት አንዱና ዋነኛው ተግባር እንደሆነም አስገንዝበዋል።