በክልሉ የቤህነን እና የጉህዴን ሰላም ተመላሾች አቀባበል ተደረገ

ታህሣሥ 28/2023 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት የቤህነን/ቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ/ እና የጉህዴን/ጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/ ሰላም ተመላሾች አቀባበል ተደረገ፡፡

የክልሉ ሰላም እንዲመለስ እልህ አስጨራሽ ጥረት በማድረግ ታሪካዊ ገድል ለፈጸሙ አካላት የምስጋናና የእውቅና መስጠት መርኃ ግብርም ተካሂዷል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ለመመለስ፣ የዜጎችን ድህንነትና አብሮነት በዘላቂነት ለመጠበቅና ለማጽናት እልህ አስጨራሽ ጥረት በመፈጸም፣ በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ የላቀ ታሪካዊ ገድል ለፈጸሙ አካላት የምስጋናና የእውቅና ተሰጥቷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ እና የተለያየ የጸጥታ መዋቅር ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።