በክልሉ የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

ሰኔ 24/2014 (ዋልታ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት በማድረግ ተጀምሯል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ፒኤችዲ) በክረምት የወጣች በጎ ፈቃድ አገልግሉት በ14 የተለያዩ ተግባራት የበጎ ፈቃድ ሥራው የሚከናወን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመርኃ ግብሩ የቤት እደሳትና ጥገና፣ የአካባቢ ጽዳት፣ የጎርፍ መውረጃዎችን ማስተካከል፣ ትምህርት ቤቶችን መጠገን፣ የችግኝ ተከላ ማከናወን፣ የገቢ አሰባሰብ እና ሌሎቹም ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 2 ሺሕ 500 የአረጋዊያን ቤቶች እንደሚጠገኑም መጠቆማቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡