በኮንታ ልዩ ወረዳ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁሉም ጣቢያዎች በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ በሚገኙ 72 ምርጫ ጣቢያዎች የተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ታዛቢዎች እና ሲቪክ ማህበራት በተገኙበት ቃለ ጉባኤ በመፈራረምና የሚጠበቁ ሂደቶችን ከፈፀሙ በኃላ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ምርጫው እየተካሄደ ይገኛል።
የልዩ ወረዳው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሲመርጡ ያገኘናቸው ነዋሪዎች የምርጫው ቀን ደርሶ በሰላማዊ ሁኔታ ምርጫው በመጀመሩ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀዋል።
የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ማልደው በመውጣት በየምርጫ ጣቢያ ሰልፍ ይዘው ምርጫውን በማከናወን ላይ ሲገኙ፣ ምርጫውን ከፈፀሙ በኋላ የችግኝ ተከላ መርኃግብር እያካሄዱ እንደሚገኙ ከልዩ ወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።