ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የሚገነባው የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል፡፡
የመስኖ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
በመስኖ ግንባታ ስራ የሚፈጠረዉ ውሃም ከመስኖ ማልማት በተጨማሪ ለአሳ ምርትና ለቱሪዝም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ነው የተባለው።
ለወይቦ የመስኖ ግንባታም 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት የተመደበ ሲሆን፣ የግንባታው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በስፍራው እየተካሄድ ይገኛል።
በማሰጀመሪያው ሥነሥረአት ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳና የኢፌዴሪ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንዲሁም የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡