በዋልታ ቲቪ ለፓርቲዎች የተመደበው ነፃ የአየር ሰዓት መጠናቀቁን የኮርፖሬቱ ምርጫ ዴስክ ገለጸ

በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተመደበው የዋልታ ቲቪ የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰዓት መጠናቀቁን የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ምርጫ ዴስክ አስታወቀ፡፡

ምርጫ ዴስኩ በዋልታ ቲቪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምረጡን ቅስቀሳ የተጠቀሙበትን ነፃ የአየር ሰዓት እና ያከራከራቸውን ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በተመለከተ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ምርጫ ዴስክ ከግንቦት 19/2013 እስከ ሰኔ 09/2013 ዓ.ም ድረስ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የተዘጋጁ የክርክር መድረኮችን ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በሁለት የክርክር ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሁለት ዙር ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን እያንዳንዳቸው ለዘጠና ደቂቃዎች ያህል አከራክሯል፡፡

በመጀመሪያ ዙር በከተሜነትና የመሰረተ ልማት ፖሊሲ ዙሪያ ብልፅግና፣ አብን፣ ኢህአፓ እና ህብር ኢትዮጵያን አከራክሯል፡፡

ወጣቶችና ሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በሁለተኛ ዙር ኢዜማ፣ ብልፅግና፣ መኢአድ ፓርቲን ምቹ መድረክ ፈጥሮ ማራከሩን ገልጿል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ምርጫ ዴስክ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ከመጋቢት 30/2013 ጀምሮ እስከ ግንቦት 19/2013 ዓ.ም ድረስ የተዘጋጁ የክርክር መድረኮችን መረጃ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

(በብርሃኑ አበራ)