በውስጧ ውስብስብና ሰፊ ችግሮችን የያዘችው አዲስ አበባ ችግሮቿን ለመፍታት በጥናትና ምርምር የተደገፈ መፍትሔ ያስፈልጋል – አቶ ዣንጥራር አባይ


ሰኔ 26/ 2013 (ዋልታ) – ዘላቂ የከተማ ልማት ለሀገራዊ አንድነትና ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዮት አዘጋጅነት አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሔደ ነው።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ዣንጥራር አባይ በውስጧ ውስብስብና ሰፊ ችግሮችን የያዘችው አ.አ ችግሮቿንን ለመፍታት ቀጥናትና ምርምር የተደገፈ መፍትሔ ያስፈልጋል ስለሆነም ይህንን ችግር ለመፍታት እንደ ስራ አመራር ኢንሰቲትዩት ያሉ ተቋማት ችግሮችን ለመፍታት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በከንቲባዋ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ያለመዘመን ችግር መከሰቱ ትልቁ ምክንያት የክህሎት ማነስ ነው ያሉት አቶ ዣንጥራር የህዝቡን ብሶት ሊፈቱ የሚችሉ ጥናቶችን የሚሰሩ ምርምሮች ከሼልፍ ላይ ወርደው መፍትሔ ሰጪ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
በኮንፍረንሱ ላይ 6 የሚሆኑ ጥናቶች እንደሚቀርብ ተጠቁሟል።
( በዙፋን አምባቸው)