በዓለም ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን የተመራ ልዑክ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገባ፡፡

ሉዑካን ቡድኑ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል ማድረጋቸውን ከክልሉ ብዙኃን መገናኛ ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን የተመራው ልዑካን ቡድን በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።