በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው

በምርጫ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና

 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዩ ኤን የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ስልጠናው በምርጫው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅም ለማሳደግ አንደሚረዳ ተናግረዋል።

ለበጎ ፈቃደኞቹ ክፍተት ባለበት ቦታዎች ላይ በተለይ በአይቲ፣ በስነዜጋ ትምህርት እና በፆታ እኩልነት ዙርያ ስልጠና የተሰጣቸው በመሆኑ ማህበረሰቡን ለማገልገል ብቁ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ቦርዱ የዘንድሮውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የተለየ ለማድረግ እና ሁሉም ዜጋ በማንነቱ ሳይገለል የእያንዳንዱ ሰው ድምፅ ትርጉም እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በቀጣይም የእጩዎች ምዝገባ እንደሚጀመር እና የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እንደሚካሄድ የገለጹት ወ/ሪት ብርቱካን፣ የምርጫ ታዛቢዎችን ገለልተኝነት የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም አመልክተዋል።

(በሄለን ታደሰ)