በዙሪያችን ያለውን እምቅ ዐቅም መለየት ወሳኙ ዕውቀት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

መስከረም 11/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዙሪያችን ያለውን እምቅ ዐቅም መለየት ወሳኙ ዕውቀት ነው ሲሉ ገለጹ፡፡

በአንድ ወቅት በጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋ ተጋላጭ የነበረው የአፋር ክልል የመካከለኛው አዋሽ አካባቢ፣ በ20 ሺሕ ሄክታር የጥጥ እርሻ ማጌጡ አዲስ ነገር ነው ብለዋል።

አካባቢው ፍራፍሬን የማብቀል ዐቅሙን እንዲገልጥ ደግሞ፣ የተሻሻለ የመስኖ  አሠራር በመተግበር ላይ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ተስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡