በደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና ጆንሰን ጁማ ኡኮት

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – በደቡብ ሱዳን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ልዑኩ አዲስ አበባ ሲገባ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና በሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡