በደቡብ ክልል 2ኛው ዙር የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት የሽኝት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – የደቡብ ክልል 2ኛ ዙር የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጣና ለማሰማራት የሽኝት ሥነ-ሥርዓት በሀዋሳ የቀድሞ ሁለገብ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት ሽኝት እየተደረገላቸው የሚገኙት የልዩ ኃይል አባላት ዝግጁነታቸውን የሚያስመሰክር ትርኢት እያቀረቡ መሆናቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ  የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።