በደብረታቦር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ጥር 24/2014 (ዋልታ) ከወልዲያ ወደ ባሕርዳር በፒካፕ መኪና ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ በደብረታቦር ከተማ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ከወልዲያ ተነስቶ ወደ ባሕርዳር ከተማ ሲጓዝ በነበረ ፒክፕ መኪና ሁለት ተጠርጣሪዎች ከ17 ሺሕ በላይ የክላሽ ጥይት እና 14 ሺሕ 6 መቶ ብር ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎቹን የደብረ ታቦር ከተማ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለው ዘለቀ ገልጸዋል።