በጅማ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተካፈሉበት የአፍጥር ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

የአፍጥር ሥነ ሥርዓት

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) በጅማ ከተማ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተካፈሉበት የረመዳን የአፍጥር ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

የአፍጥር ሥነ ሥርዓቱ “ለሀገራችን አንድነትና ፍቅር” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ተገኝ በአፍጥር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተካፍለዋል።

ሚኒስትሮቹና የሥራ ኃላፊዎቹ ዛሬ በጅማ ከተማ ጀሬን መናገሻ ላይ የሚገኘውን የንጉሥ አባጅፋርን ቤተ መንግሥት የእድሳት ሂደትን የደረሰበትን ሁኔታ ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW