በጅቡቲ ወደብ አጠቃቀም ዙሪያ የተደረገ ውይይት

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) – የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ኢ/ር የኋላሼት ጀመረ ከጅቡቲዉ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሀውመድ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀም፣ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ በቅንጅት ለመስራት እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጋራ ለመስራት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ በ10 ዓመቱ ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን በአጠቃላይ የሎጀስትክስ ጊዜና ወጪን በመቀነስ የሀገሪቱን የሎጀስቲክስ ውጤታማነትን ለማሻሻል በቅንጅትና በመናበብ መስራቱ ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።

የጅቡቲ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሀውመድ በበኩላቸው፣ የጅቡቲ መንግስትም በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት መግለጻቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል።